icono para volver a la página principal Back home

እንደ ሴት ፣ ወንድ ልጅ ወይም ታዳጊ አካል ጉዳተኛ ፣ ደህንነቴን እና እድገቴን በተመለከተ 10 መሰረታዊ መርሆዎች

1
dibujo del principio 1

እራሴን ሆኜ ነው የተፈጠርኩት እናም እንደ እርስዎም ሰው ነኝ

እንደ እርስዎ እና እንደሌሎች ሰዎች ተመሳሳይ ክብር እና ሰብአዊ መብት አለኝ:: መከበር ይገባኛል እናም ልዩነቶቼን ዋጋ እንዲሰጡ እፈልጋለሁ

2
dibujo del principio 2

ደግ እንዲሆኑልኝ ፣ እንዲወዱኝ እና ከእኔ ጋር እንዲጫወቱ እፈልጋለሁ

እርስዎም እንዲወደዱ እና በእኩልነት እንዲታዪ ይፈልጋሉ ፡፡ የእኔን ጥሩ ፍላጎቶች ከልብ ጠብቀው ህይወትን ከኔ ጋር ያጣጥሙ

3
dibujo del principio 3

ሲንከባከቡኝ፣ ሲጠብቁኝ እና ፣ እራሴን እንዴት መጠበቅ እንዳለብኝ ሲያስተምሩኝ እወዳለሁ

እኔም በራሴ መንገድ እንደዚያ እሆናለሁ

4
dibujo del principio 4

እኔን እንደ እኔ እንዲቀበሉልኝ ፣ ችሎታዎቼን እንዲያሳድጉልኝ እና ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጡኝ እፈልጋለሁ

ጥንካሬን ሲመለከቱ እና ከሌሎች ጋር እንድገናኝ ሲረዱኝ ደስ ይለኛል

5
dibujo del principio 5

እንዲያዳምጡኝ፣ ምን እየተፈጠረ እንደሆነ እንዲያብራሩልኝ እና አመለካከቴን ከግምት እንዲያስገቡ እፈልጋለሁ

ይህ ደህንነት እንዲሰማኝ እንዲሁም ለመማር እና የበለጠ እራሴን እንዳሳድግ ይረዳኛል

6
dibujo del principio 6

በእኔ ላይ ዕምነት ስለጣላችሁብኝ እና ድጋፍ ስለምትሰጡኝ ደስተኛ ነኝ

ይህን ድጋፍ ማግኘቴ በራስ መተማመን አቅሜን እንዲሁም ራስን በራስ ማስተዳደር ችሎታዬን እንዳጎለብት ያግዘኛል

7
dibujo del principio 7

ስበሳጭ ፣ ስናደድ ወይም ተስፋ ስቆርጥ ስትረዱኝ፣ ስትደግፉኝ እና ስታበረታቱኝ ደስ ይለኛል

ብዙ ጊዜ በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ውስጥ ስሆን የበለጠ ታስፈልጉኛላችሁ

8
dibujo del principio 8

ስታካትቱኝ ደስተኛ እሆናለሁ

ከእናንተ ጋር የምግባባበትን መንገድ አክብራችሁልኝ እና ድጋፍ ሰጥታችሁኝ ምቹ ፣ ሰላማዊ እና አካታች የሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ለመኖር እፈልጋለሁ

9
dibujo del principio 9

በማንኛውም አይነት ሁኔታም ሆነ ቦታ ከማንኛውም አይነት ጥቃት እንድትከላከሉልኝ እናእንድትንከባከቡኝ እፈልጋለሁ

ልክ እንደማንኛውም ሰው አካሌ፣ ነፍሴ እንዲሁም አእምሮዬ እንክብካቤ ይገባቸዋል

10
dibujo del principio 10

እኔን ማመናችሁ ለእኔ አስፈላጊ ነው

እንደ እርስዎ መታመን እፈልጋለሁ